ቅዱስ ጴጥሮስ ጊቢ ጉባኤSt. Peter Orthodox Gibi Gubae

እንኳን ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ጊቢ ጉባኤ በ ሰላም መጣቹ

Our Mission

በማህበረ ቅዱሳን ስር በመሆን በ ሰፈረሰላም ግቢ የሚማሩ ተማሪዎች የወንጌል ትምህርትን፣ስርዓትን፣ትውፊትን እንዲያውቁ እና እንዲያቆዩ በማረግ በሀይማኖቱ የፀና በምግባሩ የቀና ንቁ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ማፍራት ነው።

Our Divisions

የጊቢ ጉባኤውን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ይጎብኙ

የቋንቋ እና ልዩ ፍላጎት አገልግሎት ማስተባበሪያ ክፍል

በክፍሉ ውስጥ ያሉ አባላትን በመመደብ በተለያዩ ቋንቋዎች ትምህርትን ያሰጣል፤ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ ተማሪዎችን ድጋፍ ይሰጣል። በ ዕቅበተ እምነት ንዑስ ክፍሉ በተለያዩ እምነቶች ጫና ስር ያሉ ተማሪዎችን በመለየት አስፈላጊውን ትምህርት እና ከለላ ይሰጣል።በሀይማኖት ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ያሰጣል።

Learn more

ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል

ይህ ክፍል የግቢ ጉባኤው አባላት በሙያቸው ፣ በእውቀታቸው እንዲሁም በጉልበታቸውን ቤተ ክርስቲያንን እና ልጆቿን የሚያገለግሉበትን ሁኔታዎችን ያመቻቻል። _በተጨማሪም መጽሐፍትን ለተማሪዎች ተደራሽ ማድረግ፣ የግቢ ጉባኤው አባላት በቀለም ትምህርታቸው እንዲጠነክሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በሲኒየር ገለጻ orientation በማዘጋጀት የፈተና ወረቀቶችንና ሃንዳውቶችን ማሰባሰብ እና ተደራሽ ያደርጋል ።

Learn more

መዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል

የግቢ ጉባኤው አባላት በተለያዩ የግቢ ጉባኤው መርሐ ግብራት ላይ መዝሙራትን እና የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን በማቅረብ አባላት ሕይወት ተኮር እና እውቀት ተኮር ትምህርቶችን እንዲቀስሙ የሚያደርግ ክፍል ነው፡፡ እንዲሁም -የተውኔት፣ የግጥም እንዲሁም ሥነ-የሰዕል ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚያደረግ ክፍል ነው። - ወረብ በልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ላይ ያስጠናል -በገና እና ከበሮን ተማሪዎችን ያሰለጥናል።

Learn more

ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል

የግቢ ጉባኤያት አባላት በቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ ጎልበተው ለራሳቸው ከፍ ብሎም አጠገባቸው ላለው ሰው ሲልቅም ለቤተክርስቲያን ጋሻ ሆነው ከአጽራረ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ራሳቸውን ጠብቀው ትክክለኛይቱን የሐዋርያት ትምህርት እንዲያውቁ እናም በተግባር እንዲኖሩበት የሚያበረታታ እና የሚያስገነዝብ ክፍል ነው በተጨማሪም አብነት ትምህርትንም ያሰጣል።

Learn more

Upcoming Events

Join us for our weekly services and community events

የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ 13ኛ አመት የምስረታ በዓል

June 7, 2026

Time: ከ 7:30 ጀምሮ

Location: ደ/ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ቤ/ክ

እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ግቢ ጉባኤያችን የተመሰረተበትን 13ኛ ዓመት የልደት በዓል በውጪም በውስጥም ያሉ ከምስረታው አንስቶ እስከዛሬ ድረስ እንደዋርካ እየሰፋ በመጣው አገልግሎት የማኅበሩ አባል የሆኑ ቤተሰቦቹን በማሰባሰብ በታላቅ ድምቀት ግንቦት 30 ይከበራል

Join Our Community

የተለያዩ መረጃዎችን እና ስለ ጊቢ ጉባኤው በደንብ ለማወቅ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።