About
ስለ ጊቢ ጉባኤው ታሪክ እና አስተዳዳሪዎች ለማወቅ
የግቢ ጉባኤያችን ታሪክ በአጭሩ
በ 2003 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ጤና ሳይንስ ተማሪዎች አዲስ ካምፓስ እንዲገቡ ተደረገ። የገቡበትም ካምፓስ አሁን ላይ ሰፈረ ሰላም በመባል የሚታወቀው ግቢ በመጀመሪያ ሲመሰረት (በተለምዶ ሳንባ ነቀርሳ) ሕክምና ማዕከል የነበረው የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ግቢ ነበር። ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ከጀመረ ከ 2 ዓመት በኋላ በ 2005 ዓ.ም ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ ሲሆን የመመስረቱ ምክንያትም ከዛ በፊት የግቢው ተማሪዎች በጳውሎስ ግቢ ጉባኤ ይገለገሉ የነበረ ቢሆንም ሁለቱ ተማሪዎች የሚሳለሙበት ደብር የተለያየ በመሆኑና ካምፓሱ በደንብ ራሱን በመቻል ተማሪዎችን ማስተማር በመጀመሩ ነው።
ግቢ ጉባኤው ራሱን ለመቻል ጥያቄውን ለማኀበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማዕከል አቅርቧል። ሚያዚያ 2004 ዓ.ም ከማዕከል በወጡ ተጠሪዎች አሰባሳቢነት ስለግቢው አጠቃላይ ሁኔታና ቀጣይነት ከተመረጡ ልጆች ጋር ውይይት ተካሂዶ ግቢው ከ ቀጣይ 2005 ጀምሮ ራሱን ችሎ ሥራ እንዲጀምር ከስምምነት ተደርሷል። ስሙም ቅዱስ ጴጥርስ ተብሎ እንዲቀጥል ሆኗል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተማሪ ቁጥር እጅጉን ጨምሮ ግቢ ጉባኤያችን እያደገ በመምጣት የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል። ከነዚህም ውስጥም ኮርስ፣ የአብነት ትምህርት፣ የጸሎት እና የአንድነት መርሐግብራት፣ የበገና ትምህርት፣ ዝክረ ቅዱሳን እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

Our Journey
ምስረታ
ቅ/ጼጥሮስ እውቅና አጊኝቶ ተመሰረተ ኮርስ፣ፅዋ እና ልዩ መርሐ ግብራት ተጀመረ አብነት ትምህርት ቤት ተቆቆመ መንፈሳዊ ጉዞ
መንፈሳዊ ጉዞ
መደበኛ መርሐ ግብራት መጠናከር የተማሪ ቁጥር መጨመር መንፈሳዊ ጉዞ
ገቢ ማስገቢያ ስራዎች
ለግቢው ገቢ የሚያስገኙ ቆሚ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ተንቀሳቅሷል።
ዜማ ትምህርት ቤት
አብነቱን በማጠናከር የቁጥር እና ዜማ ት/ቤት ማስከፈት ተችሏል። ኮርስ በኦሮሞኛ መስጠት ተችሏል። የቤተሰብ ምደባ ተጀምሯል። መንፈሳዊ ጉብኝቶች
ስልጣነ ክህነት
ለ ሰባት ተማሪዎች ስልጣነ ክህነት ማሰጠት ችሏል። መደበኛ መርሐ ግብራት መጠናከር መንፈሳዊ ጉዞ
መርሀ ግብራት መጠንከር
መደበኛ መርሐ ግብራት መጠናከር መንፈሳዊ ጉዞ
የቤተሰብ መዋቅር
የቤተሰብ መዋቅር በአዲስ መልክአደራጅቶ መንቀሳቀስ ተችሏል። መደበኛ መርሐ ግብራት መጠናከር መንፈሳዊ ጉዞ
በገና ትምህርት ቤት
4ተተኪ መምህራን በደረጃ 1 እና 1ተማሪ በደረጃ 2 አሰልጥኗል የበገና ትምህርት ቤቱን አስከፍቷል።
መምህራን ስልጠና
8 በደረጃ 1 ተተኪ መምህራንን አስመርቆል ቅዱሳት መካናት ጉብኝት
ኮርስ በተለያዩ ቋንቋዎች
ሎከር ማሰራት ተችሏል የ ቅድሳት ስዕላት እና በገና ግዢ ተደርጓል በተለያዩ ቆንቆዎች ኮርስ ተሰጥቶል
Our Leadership
ጊቢ ጉባኤው ሳይስተጓጎል ስራውን እንዲያስኬድ እያደረጉ ያሉ አመራሮች

የ 2016 ስራ አስፈፃሚዎች
አገልጋዮች
በ 2016 ላይ ጊቢ ጉባኤው ስራውን ያለማቋረጥ እንዲያደርግ ሲሰሩ የነበሩ አገልጋዮች።

የ 2017 ስራ አስፈፃሚዎች
አገልጋዮች
በ 2017 ላይ ጊቢ ጉባኤው ስራውን ያለማቋረጥ እንዲያደርግ ሲሰሩ የነበሩ አገልጋዮች።
Our Beliefs
The core tenets of Orthodox Christianity that guide our faith and practice
The Holy Trinity
We believe in one God in three persons: Father, Son, and Holy Spirit.
Jesus Christ
We believe that Jesus Christ is the Son of God, fully divine and fully human, who became incarnate for our salvation.
The Holy Spirit
We believe in the Holy Spirit, who proceeds from the Father, who together with the Father and the Son is worshipped and glorified.
The Church
We believe in one, holy, catholic, and apostolic Church, which is the body of Christ.
The Sacraments
We believe in the seven sacraments as channels of God grace in our lives.
The Scriptures
We believe the Holy Scriptures to be inspired by God and a faithful witness to His revelation.
These beliefs are rooted in the ancient traditions of the Orthodox Church, passed down through generations of faithful Christians. We invite you to learn more about our faith by attending our services and educational programs.